Charity, Vaccine

ታላቅ የበረከት ጥሪ ከኩክ የለሽ ማርያም ገዳም!

በመላው አለም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እንኳን ለ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ የምትገኘውና በድንቅ ተዓምራቷና ፈዋሽነቷ በአለም የምትታወቀው ታሪካዊቷ የኩኬለሽ ቅድስት ማርያም ገዳም፤ በአባ ኃ/ጊዮርጊስ አማካኝነት 14 አመታትን ጊዜ ፈጅቶ በ4 ፍልፍል ዋሻ አብያተ ክርስቲያናትና በ1 ቤተክርስቲያን እንደተገደመች ይነገራል።

እነሆ በፍልፍል ዋሻዎቹ ላይ በተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ምክንያት በቤተክርስቲያኗ አቅም ሊቀለበስ የማይችል የመደርመስና የመሰንጠቅ አደጋ ተደቅኖባታል።

በገዳሟ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል እጅግ ጥንታዊና ታሪካዊ በሆነው ሳሪያን ቅዱስ ሚካኤል በአመታዊ ክብረ በዓሉ ቀን፣ ሰኔ 12/2017 ዓ/ም የሐገራችን ተጋባዥ እውቅ አባቶች ዘመሪያንና የቤተክርስቲያን አገልጋዎች በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።

በተያያዘም ከሰኔ 13/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በTTV ኢትዮጵያ፣ በራማ ሚዲያ፣ በ ወለተማርያም ሚዲያ፣ በአዝኤል ሚዲያ፣በኢቲ አር ቲ ሚዲያ፣ በምርኩዝ ሚዲያ፣ በሰሚያት ሚዲያ፣ በአቡቀለምሲስ ሚዲያ እና በሌሎችም ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነት ባለቸው የመገናኛ ብዙሀን ተቋማትና ታዋቂ ግለሰቦች አማካኝነት የእናታችን የኩኬለሽ ማርያም ገዳም የቅርስ መልሶ መጠገን ድጋፍ የቀጥታ ሥርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ይካሄዳል።

እኛም በንግሥ ክብረ በዓሉና በጉባኤው በመገኘት፣ እንዲሁም የቀጥታ ሥርጭቱን በመደገፍና ለ አለም እንዲደርስ በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ገዳሟ ጥሪዋን ታቀርባለች።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
09 61 82 00 00
09 61 83 00 00
09 61 84 00 00

ይደውሉ።

ኑ አባቶቻችን ያቆዩልንን የእመቤታችንን ቤት ዳግም ወደነበረበት እንመልስ!

የኩክ የለሽ ማርያም ገዳም አስተዳደር!

Leave A Comment

Your Comment
All comments are held for moderation.